አሻራ

በያዝነው ሳምንት 79ኛው የድል ቀን የመታሰቢያ በዓል ታስቦ ይውላል። ሚያዝያ 27 ከየካቲት 23 በዓድዋ ድል ከተገኘው አኩሪ ታሪክ የማይተናነስ ለኢትዮጵያን የላቀ ትርጉም ያለው መታሰቢ በዓል ነው።ስርዓቱና ደጋፊዎቹ በሚፈጥሯቸው ተልካሻ ጉዳዮች ላይ ተጠምደን “አባቶቻችን” በዱር በገደል ብለው ደምና አጥንታቸውን መስዕዋት አድርገው ዛሬ ከባዕድ የሥነ_ልቦና ባርነት የጠበቀንን አኩሪ የድል የመታሰቢያ በዓላችንን “ከዓድዋ” ባልተናነሰ መልኩ ልንዘክር ይገባናል። የዓርበኝነቱ ተዋናዮችንም
Ø እነ አበበ አረጋይ

Ø በላይ ዘለቀ

Ø አቡነ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም የድሉ መሪና ተሳታፊ የነበሩትን የታሪክ ፈርጦቻችን በሚቀጥሉት ቀናት እንዘክራለን።

ለዛሬ ሚያዝያ 27ን በአጭሩ እንዲህ እንመለከታለን፦
በጣሊያን የወረራ ዘመን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዋ ከታጠፈ ፣ ሉዓላዊነቷ ከተደፈረ 5 ዓመታት በኋላ ነፃነቷን ካስመለሰች ከ3 ቀን በኋላ 76 ዓመት ይሞለዋል። ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ንጉሰ_ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአርበኞች ብርታትና መስዋዕትነት የጣሊያን ባንዲራ አውርደው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በታላቁ ቤተ-መንግሥት ሰቀሉ፡፡ ጣሊያን ከአድዋ ሽንፈት 40 ዓመታት በኋላ በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በወታደራዊ ኃይል ይበልጥ ተደራጅቶ ኢትዮጵያን ከሦስት አቅጣጫዎች ወረረ፡፡ከአድዋው ዘመቻ ያልተሻለ የጦር ትጥቅ የነበራት ኢትዮጵያም የጣሊያንን ጦር ለ8 ወራት በፅናት ተዋጋች፡፡

የጊዜዎቹ ኃያላን እንግሊዝና ፈረንሳይ የጦር መሣሪያ በግዢ እንዳታገኝ ለጣሊያን ተደርበው ስላሴሩባት ኢትዮጵያ ብቻዋን ጦርነቱን በመጋፈጧ ድል ማግኘት አልቻለችም፡፡
የየግንባሮቹ የኢትዮጵያ የጦር አዛዦች ብዙዎቹ ሞተው ሠራዊቱም በአውሮኘላን ቦምብ ተደብድቦ ያለቀው አልቆ የቀረው ቀርቶ ጣልያን ጊዜያዊ ድል አግኝታ አብይ አብይ ከተሞችን ብትቆጣጠርም ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በገጠሩ ክፍል እምቢ ለነፃነቴ ፣ እቢ ለአገሬ ብለው የሽምቅ ውጊያ ጀመሩ፡፡ ንጉሰ ነገስቱም ስደት ሄደው በጊዜው ለነበረው የመንግሥታቱ ማኅበር /ሊግ ኦፍ ኔሽንስ/ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ የሚሰማቸው ግን አላገኙም፡፡

አርበኞች ግን ከቀን ወደ ቀን ድል እየተቀናጁ የጣሊያን ወታደሮችን መፈናፈኛ ፤ መግቢያ መውጫ አሳጧቸው፡፡
ከጣሊያን ወታደሮች ይማርኳቸው በነበሩ መሣሪያዎች ራሳቸውን እያደራጁ አብዛኛውን የገጠር ክፍል ተቆጣጠሩ፡፡

የ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጣሊያን የናዚ ጀርመን አጋር ሆነች፡፡ ያን ጊዜ እንግሊዞች የጣሊያን ጠላት ሆነው ኢትዮጵያን መደገፍ ጀመሩ፡፡ ስለዚህም ወታደራዊ ድገፍ ሰጥተው ፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ረዷቸው፡፡

በጄኔራል ካኒንግሂም የሚመራው የእንግሊዝ ጦር ከኬንያ ተነስቶ ከደቡብ አቅጣጫ ወደ መሀል ኢትዮጵያ ሲገሰግስ ፤ በጄሪራል ኘላት የሚመራው ጦር ከሱዳን ተነስቶ ወደ አሥመራ ፤ ከዚያም ከሰሜን አቅጣጫ ወደ መሐል ኢትዮጵያ ተንቀሳቀሰ፡፡

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የሚመራውና የአርበኞችና የእንግሊዝ አማካሪዎች የሚገኙበት ጌዲዮን ተብሎ የተሰየመው ጦር ከሱዳን ተነስቶ በኦሜድላ አልፎ በጐጃም በኩል ወደ መሐል አገር ገሠገሠ፡፡

በመካከለኛ ኢትዮጵያ አርበኞች በጣሊያን ወታደሮች ላይ ጥቃትቸውን አፋፋሙ፡፡ ጣሊያኖች ክፉኛ ተሸነፉ፡፡ በየቦታው ድል የመሆናቸው ዜና ተነገረ፤ ዘመቻው ከተጀመረ 2 ወራት ሳይሞላው ፤ ጣሊያኖች አዲስ አበባን ለቀው ፈረጠጡ፡፡

መጋቢት 28/1933 ዓ.ም የጄኔራል ካኒንግሃም ጦር አዲስ አበባን ተቆጣጠረ፡፡ እንግሊዞች ኢትዮጵያውን አርበኞች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ስላልፈለጉ ቀዳማዊ ኃይል ሥላሴን በደብረ ማርቆስ ለአንድ ወር ያህል እንዲቆዩ አደረጓቸው፡፡

ይሁንና በአዲስ አበባ በአርበኞች ተፅዕኖና ቅሬታ የተነሳ አርበኞች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ፈቀዱ፡፡ አፄ ኃይለ ሥላሴም ወደ አዲስ አበባ እንዲጓዙ ፈቀዱ፡፡ ንጉሰ ነገስቱም ሚያዚያ 27 በአዲስ አበባ ታላቁ ቤተ-መንግሥት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሰቀሉ፡፡

በአርበኞች ታላቅ ተጋድሎ፤ ኢትዮጵያ በዓለም ፊት በልጆቿ መስዋዕትነትና የደም ማኅተም ነፃነቷን አፀናች፡

ክብር ኢትዮጵያን በክብር ላቆዩን አባት አርበኞቻችን!!

 

 

በኑረንበርግ የኢትዮጵያውያን ባህል ማህበር (ኮሚኒቲ) የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ                     ቀን 29/03/2019 

                                                    
በኑረንበርግ የኢትዮጵያውያን ባህል ማህበር (ኮሚኒቲ) አስተባባሪነት ነዋሪነታቸው በኑረንበርግና አካባቢዋ የሆነ በርካታ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በ 24.03.2019 ከቀኑ 15 ሠዓት ጀምሮ Wiesenstr. 86 በሚገኝው የስብሰባ አዳራሽ በመገኝት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሃገራችን ክፍሎች ሰው ሰራሽ በሆኑ ግጭቶች ከቀያቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ችግር ለተዳረጉ ወገኖቻችን ዕርዳታ የማሰባሰብ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፈዋል።  
በዚህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራምና በቀጠሉት ቀናት በዕለቱ ለመታደም ካልቻሉ የከተማችን ኢትዮጵያውያን እስከ አሁን በድምሩ € 6745,0 ኦይሮ ማሰባሰብ የቻልን ሲሆን ይህም እርዳታ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ለተጎጂዎች እንዲደርስ ይህንን ግብረ ሠናይ ስራ ከጅምሩ ላስተባበረው ግሎባል አሊያንስ እንዲደርስ እምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን። በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለተባበራችሁን ሁሉ በተረጂዎች ስም በድጋሚ ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን። 
በእለቱ በአዳራሹ ተገኝቶ እርዳታ ማሰባሰቡ ላይ ከተሳተፈው ሕዝብ ጋር ካደረግነው ሠፊ ውይይትና ታዳሚው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንዲደርስ ከሚፈልገው መልዕክት በመነሳት የሚከተለውን የአቋም መግለጫ እናቀርባልን። 
 
                                                      የአቋም መግለጫ 
 እንደሚታወቀው ማህበራችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በማህበራዊና በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ትንሽ የማይባል እንቅስቃሴ  ሲያድርግ ቆይቷል፤ በማድረግ ላይም ይገኛል፤ወደፊትም እንደ አንድ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ማህበር የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ አቅም በፈቀደ መጠን ለመወጣት ይጥራል። በኢትዮጵያ የመጣውን የለውጥ ጅማሮምና አራማጁንም የለውጥ ሃይል  በአለን አቅም ሁሉ እየደገፍን እንገኛለን። ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ውስጥ እየታዩ ያሉ ዜጎችን ያለ አግባብ ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው የማፈናቀል የሰብአዊ መብት ጥሰትን ያካተቱ አድልኦ የሚስተዋልባቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ መምጣቱ ስላሳሰበን ከማህበራችን አባላትና ከአካባቢው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ጋር በመመካከር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል።  
  
1. በወገኖቻችን በማንነታቸው ምክንያት ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው እና ደክመው ለፍተው ካፈሩት ቤት ንብረታቸው ላይ  እየደረሰ ያለውን ማንኛውንም ማፈናቀል እና የዜግነት መብት ጥሰቶች አጥብቀን እናወግዛለን።    

 

2. በልማትና ህግ ማስከበር ሽፋን የሚደረጉ ኢሰብአዊ ማፈናቀሎች እንዲቆሙ እንጠይቃለን። ለልማት ተፈላጊ ቦታዎች ዜጎችን በማፈናቀልና  ጎዳና ላይ በመበተን ሳይሆን በዓለም ዙሪያ እንደሚተገበረው በህጋዊ መንገድ ተመጣጣኝ ካሳ በመስጠት፣ ሌላ ተተኪ የመኖሪያ ቦታ በማዘጋጀትና ከልማቱም ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር በማመቻቸት መሆን ይኖርበታል። ይህ ሁሉ ባልሆነበት ሁኔታ የሚደረጉ ማፈናቀሎች ትልቅ የሰብአዊ መብት ጥሰት ስልሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን። ይህንንም ተግባር የሚፈጽሙ የመንግስት ሀላፊዎችና የድርጊቱ ተባባሪዎች በህግ ተጠያቂ የሚሆኑበት አግባብ እንዲመቻች እንጠይቃለን።    

3. ለዘመናት በመተሳሰብና በጋራ የኖረውን ኢትዮጲያዊ፣ጎሳ ተኮር የሆነ የጥላቻን መንፈስ በመስበክ ህዝብን ለከፋ እልቂት ለመዳረግ በፖለቲካ ስም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችንና ተቋማትን መንግስት በህጋዊ መንገድ ለሚፈፅሙት ሃገርን ጎጂና ህገ ወጥ እንቅስቃሴ መጠየቅም እንዳለ እንዲያሳይ እንጠይቃለን።

 4. አዲስ አበባንም ሆነ ሌሎችን የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በስብጥር የሚኖሩባቸውን ትላልቅ የኢትዮጵያ ከተሞች የአስተዳደርና የባለቤትነት ጥያቄ በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች የሁሉንም ነዋሪዎች ፍላጎቶችና ጥቅሞች ባማከለ መንገድ ሊፈቱ የሚችሉት በስሜትና በሆይሆይታ ወይንም በጉልበት አለኝ አመንክዮ ሳይሆን ከትክክለኛው የፌደራሊዝም ፅንሰ ሃሳብ ትግበራ ጋር ተያይዞ በጣም በብዙ ሃገሮች ላይ ከተተገበሩ አዎንታዊ ልምዶች ትምህርት በመውሰድ ከሚዘረጋ ለሁሉም ያገሪቱ ዜጎች ፍትሃዊ ከሆነ አሰራር ነው ብለን እናምናለን።  በነዚህ ከተሞች ላይ ለብቻው የባለቤትነት መብት ሊኖረው የሚችል አንድ ግሩፕ ሊኖር እንደማይችልና፣የዚህ አይነቱ አመለካከት በሕዝቦች አብሮነት ላይ ከሚፈጥረው አሉታዊ ተፅዕኖ በመነሳት አጥብቀን የምንቃወመው መሆናችንን እንገልጻለን።      

5. ዜጎች ተፈጥሮሃዊና ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተከብሮ ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ በመረጡበት ስፍራ የመኖር፣ የመስራትና ንብረት የማፍራት መብታቸው መጠበቅ አለበት። ሁሉም ሕዝባችን መንግስት ይህን የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ግደታውን በአግባቡ ለመወጣትና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያለ ምንም ስጋት በሃገሩ በነጻነት የመኖር ዋስትናው እንዲረጋገጥለት በሚያደርገው ጥረት ሙሉና ልባዊ ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ አበክረን እንጠይቃለን።

 6. ወጣቶቻችን ማስተዋል የሚገባቸው አብዛኛው ህዝብ ዘሩ ሳይለይ በመሠረታዊ የሕክምና ግልጋሎት እጦት ህይወቱ የሚቀጠፍባት፣ ሊያጣሉን የሚከጅላቸው ከተሞቻችን በአየር ብከላ ምክንያት ገና እንደ ልብ ንጹህ ዓየር እንኳ የማይተነፈስባቸው፣ ብዙ ህፃናት ዘራቸው ሳይለይ በህፃናት መዋያና በጥሩ ትምህርት ቤቶች ታንፀው የማድግ ዕድል ያልተረጋገጠባት አገር እንዳለችን ነው። ይህንን ዕውነታ ለመለወጥ ጥሩ አለም አቀፋዊና አገራዊ ድባብ በሚስተዋልበት በዚህ የታሪክ አጋጣሚ አጣናና መትረየስ እየተሸከሙ ከተማ ማጥለቅለቅ ሃገራት የሚያነጥፉላቸውን ቀይ ምንጣፍ ከሚያማርጡ ስራና ሃብት ፈጣሪ ኢንቨስተሮች ዘንዳ የመመርጥ እድል አሳጥቶ የሕዝባችን የሰቆቃ ኑሮ እንዲራዘም ከማድረግ ውጪ የሚያመጣው ፋይዳ እንደሌለ ነው። የራሳችሁም የወደፊት ዕድል ሠላሟ ከተጠበቀ፣ የተረጋጋ ኑሮ፣ የትምህርትና የሥራ ዕድል ልትፈጥር ከምትችል ሃገር ጋር እንደሚቆምና እንደሚወድቅ በነገሮች ሁሉ ላፍታም እንዳትዘንጉት እንመክራለን።        
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!!!

ኢትዮጵያ ሃገራችን ለዘላለም ትኑር!!! 
 
በኑረንበርግ የኢትዮጵያውያን ባህል ማህበር (ኮሚኒቲ) 

በቀን 1ኦይሮ ለኢትዮጵያችን

የኑረንበርግ ኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድን ወገናዊ ጥሪ በመቀበል ከኦክቶበር ወር 2018 ጀምሮ ወደ ተግባራዊ ስራ ገብቶ ተሳታፊዎችን በማነሳሳት፣ ቀላልና ትራንስፓረንት የአሰባሰብ፣ የዶኩመንት ማድረጊያና የመላኪያ መንገድ በመዘርጋት ከአንድ አገር ወዳድ ማህበር የሚጠበቀውን የሃላፊነት ስራ በመወጣት ላይ ይገኛል። እርስዎም በዚህ ለወገንና ሃገር ጠቃሚ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ለመሆን አሁኑኑ ይቀላቀሉን።

 

ታላቅ በሰላምና በፍቅር የመደመር ቀን ለኑረንበርግና አካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሙሉ

ተቃርኖ
Vorbereitungsworkshop

ሰዎች ብዙ ስለ ተቃርኖዎች ያወራሉ …  አምላክ የፈጠረው ግን ብዝሃነትን ነው።. የኑረንበርግ ኢትዮጵያውያን ባህል ማህበርና የቱርክ ኩርዶች የወጣቶች ድምፅ ማህበር ቀለማትንና ጣእማትን እንድ ምሳሌ በመጠቅም ይህንን የተፈጥሮ እውነታ ያሳያሉ።  የተለያዩ ቀለማትና ጣእሞች ተደምረው የሚያፈዝ ውበት እንዲሁም እጅ የሚያስቆረጥም ምግብ ይፈጥራሉ!

ተቃርኖ
የተቃርኖ ሁለተኛ ዎርክ ሾፕ በኢትዮጵያውያን ባህል ማህበር ከኤፍ ሲ ዋልያ ኳስ ተጫዋቾች ጋር

በ 11082018 የኑረንበርግ ኢትዮጵያውያን ባህል ማህበር ከዋልያ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾች ጋር በመሆን ባዘጋጀው ያንድ ቀን ዎርክ ሾፕ አዲሱ የመላመድ ድንክዋን ሽፋን ተጨማሪ ውበትና የመልእክት ማስቀመጫ ቦታ አገኘ። ልዚህም 105 ትሪአንግሎች መሃላችው ላይ ክብ ነጭ ሰርክሎች ተትተው እነዚህ ላይ ተሳታፊዎች ወይንም ታዳሚ እንግዶች አስፈላጊ ወይንም ጠቃሚ የሚሉትን መልእክት በማስተላለፍ በቀጥታ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይደረጋል።