የዚህ ድሕረ ገጽ ተልዕኮ

ጤና ይስጥልን,  ወደ ድህረ ገጻችን እንኳን ደህና መጡ!

 

ከ 1980 ዎቹ የመጨረሻ ዓመታት ጀምሮ ቁጥራቸው በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ኢትዮጵያውያን በኑረንበርግና አካባቢው ይኖራሉ። እንደየዝንባሌዎቻቸውና እምነታቸው በተለያዩ ማህበራት፣የዕምነት ቤቶች ወይም የፍላጎት ቡድኖች በመሰባሰብ ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ባህላዊ ሕብረ ቀለማዊነት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። የዚህ ድህረ ገጽ ተልዕኮ የነዚህን የተለያዩ ኢትዮጵያውያን እንቅስቃሴዎች ሰብሰብ ባለ መልኩ ማስተዋወቅ፣ በተወሰነ ደረጃ ቢራራቁም ተመሳሳይ ስነልቦናም  ሆነ የኑሮ ተግዳሮቶቸ የሚጋሩትን ያንድ አገር ልጆች እንቅስቃሴዎች መቃኛ መድረክ መሆንና ከፍ ሲልም በኢትዮጵያውያኑ መሀከል መናበብንና መቀራረብን ማበረታታት ነው።

ድህረ ገፃችን ላይ መልካምና አስገንዛቢ ቆይታን እንመኝልዎታለን!